ስለዚህ ልብስ
ቀዳዳማው አሠራር አየር ስለሚያስገባ በፀሐይ ቀዝቃዛ ነው፤ በቀላል ቲሸርት ላይም ሆነ ብቻውን ያምራል። ከትከሻ እስከ ጫፍ አራት ክፍሎች ይወርዳሉ፦ ጥቁር፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ፤ ጥቁር ኮሌታና አጭር የቪ መክፈቻ አለው።
ለወንድም ለሴትም የሚሆን ሰፋ ያለ ልክ ነው። የተለመደ መጠንዎን ይዘዙ፣ ወይም «Custom» መርጠው ልኬትዎን ለሰላማዊት ይንገሯት።
የተሠራበት
ለስላሳ አክሪሊክ ክር
አያያዝ
በቀዝቃዛ ውሃና በለስላሳ ሳሙና በእጅ ይጠቡ። ውሃውን በቀስታ ይጫኑት፤ አይጠምዝዙት። በጥላ ሥር በጠፍጣፋ ቦታ ዘርግተው ያድርቁ፤ እርጥብ እያለ ቅርጹን ያስተካክሉ። አይስቀሉት፣ በማድረቂያ ማሽን አያድርቁት፣ በካውያ አይተኩሱት።















